Projects

News

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ!!

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ!! በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሸን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ደንበኞቹን ለማርካት፣ ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት እና ከደረጃ በታች የሆኑ ስራዎች ጋር ባለመደራደር በአለም ላይ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ደረጃዎች የሚያሟሉ ሲሚንቶ እና ተዛማጅ ምርቶችን አምርቶ በማቅረብ በISO 9001:2015 የጥራት ስራ አመራር ሰርተፊኬት ጥራታቸውን ጠብቆ በሚያመርታቸው እና በሚያቀርባቸው OPC (42.5 N) እና PPC (32.5 N) ከእ.ኤ.አ ህዳር 28/2025 ጀምሮ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይ የጥራት አስተዳደር ስርዓት መመሪያ መርሆችን በመጠቀም ሙሉ በሙሉ የደንበኞቹን ፍላጎት በማሟላት፣ በየደረጃው መፍትሄ በመስጠትና በማገልገል ሃላፊነቱን ያረጋግጣል፡፡

የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ድረስ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ አፈጻጸም ብቃት!” (Quality: From Compliance to performance) በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን እና የፍተሻ ላብራቶር ላይ ተሳትፎ በማድረግ እንዲሁም የብር ስፖንሰር በመሆን ላደረገው አስተዋፅዖ የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡Dec...9/2024