News
የአረንጓዴ ዐሻራ
ዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ 800 ሚሊዮን ችግኞችን በሃገር አቀፍ ደረጃ ሀምሌ 27 ቀን 2018 ለመትከል በተያዘው መርሀ ግብር መሰረት በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የፋብሪካው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአደአ በርጋ ወረዳ አስተዳዳሪዎች፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የፋብሪካው ሰራተኞች በተገኙበት የተለያዪ ችግኞችን በፋብሪካው ጊቢ ውስጥ በማፍላት/በማዘጋጀት የመትከል ስራ ተከናውኗል፡፡ እንዲሁም በታጠቅ ቅርንጫፍ የኮርፓሬሸኑ እና የፋብሪካው አመራሮች እና ሰራተኞች ችግኝ የመትከል ስራው ላይ ተሳትፈዋል። በተጨማሪም በሙገር አካባቢ ለሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች በጃሊሳ ችግኝ ጣቢያ ከተዘጋጁት ውስጥ ብዛታቸው 144,870 የተለያዩ ችግኞችን በነፃ ለማከፋፈል የተቻለ ሲሆን ይህም የችግኝ ዓይነት እና ብዛት .ቡና=25,200 ፣ ሎሚ=6,800፣ ፓፓያ=11,450፣ ግራቪሊያ=70,000፣ ዘይቲን=15,340 እና ግሽጣ=16,080 ናቸው።

















የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ
የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ዛሬ ሚያዝያ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ተከፍቷል:: በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፓሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኤክስፓ ተካፋይ በመሆን ምርቶቹን ለተጠቃሚዎች በማስተዋወቅ ይገኛል።




ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ!!
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ሰርተፊኬት ባለቤት ሆነ!! በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሸን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ደንበኞቹን ለማርካት፣ ለሀገሪቱ ዘላቂ ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት እና ከደረጃ በታች የሆኑ ስራዎች ጋር ባለመደራደር በአለም ላይ ብቁ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሁሉንም አስፈላጊ የሆኑ ደረጃዎች የሚያሟሉ ሲሚንቶ እና ተዛማጅ ምርቶችን አምርቶ በማቅረብ በISO 9001:2015 የጥራት ስራ አመራር ሰርተፊኬት ጥራታቸውን ጠብቆ በሚያመርታቸው እና በሚያቀርባቸው OPC (42.5 N) እና PPC (32.5 N) ከእ.ኤ.አ ህዳር 28/2025 ጀምሮ ባለቤት መሆን ችሏል፡፡ ፋብሪካው በቀጣይ የጥራት አስተዳደር ስርዓት መመሪያ መርሆችን በመጠቀም ሙሉ በሙሉ የደንበኞቹን ፍላጎት በማሟላት፣ በየደረጃው መፍትሄ በመስጠትና በማገልገል ሃላፊነቱን ያረጋግጣል፡፡



የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ድረስ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ አፈጻጸም ብቃት!” (Quality: From Compliance to performance) በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን እና የፍተሻ ላብራቶር ላይ ተሳትፎ በማድረግ እንዲሁም የብር ስፖንሰር በመሆን ላደረገው አስተዋፅዖ የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡Dec...9/2024



