RECENT EVENTS
የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባላትና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች የመሰክ ጉብኝት በሙገር
የኮርፖሬሽኑ ቦርድ አባላትና የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የመስክ ጉብኝት በማድረግ ፋብሪካው ያለበትን ቴክኒካልና ቴክኖሎጂካል ችግሮች እንዲቀረፉ ድጋፍ ለማድረግና ምርታማነትን ለማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከፋብሪካው አመራሮችና የሠራተኛ ማህበር ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገዋል። ታህሳስ 11/2017 ዓ.ም
የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት
በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ከህዳር 26-28/2017 ዓ.ም ድረስ “ጥራት፡ መስፈርቶችን ከማሟላት ወደ ላቀ አፈጻጸም ብቃት!” (Quality: From Compliance to performance) በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ኢግዚቢሽን እና የፍተሻ ላብራቶር ላይ ተሳትፎ በማድረግ እንዲሁም የብር ስፖንሰር በመሆን ላደረገው አስተዋፅዖ የምስክር ወረቀት ተበርክቶለታል፡፡Dec...9/2024
ለክቡራን ለደንበኞቻችን እና ባለድርሻ አካላት፡፡
ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በ3ኛ መስመር ላይ አጋጥሞት የነበረውን ችግር በማኔጅመንቱ እና በሰራተኛው ከፍተኛ ጥረት ጥገናው በተሳካ ሁኔታ በመጠናቀቁ እና ፋብሪካው ወደ ማምረት ሥራ በመመለሱ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ገዛኸኝ ደቻሳ በጥገናው ላይ ለተሳተፉት የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ምስጋና በማቅረብ የምሣ ግብዣ አድርገዋል፡:nov 25/2024
ፋብሪካችን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ተሸላሚ ሆኗል
አቢሲኒያ የኢንድስትሪ ሽልማት ድርጅት የተለያዪ ድርጅቶችን የአሸናፊዎች አሸናፊ ባዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል የሽልማት ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ በርካት ድርጅቶች ተሸላሚ ሲሆኑ ከነዚህ ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት ድርጅቶች አንዱና ብርቅዬ ፋብሪካችን ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ውስጥ ከጠንካራ ሰራተኞች፣ ቡድን መሪዎችና ከፍተኛ አመራሮች መካከል የወርቅ ሜዳሊያና የዲፕሎማ ሽልማት ያስመዘገበ ሲሆን ድርጅታችን በተደረገው የሽልማት መስፈርት መሰረት የረጅም ዓመት አገልግሎትና ከፍተኛ ካፒታል ካስመዘገቡት መካከል 2ኛ በመውጣት የኢንድስትሪ ሽልማት ፕሮግራም ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋንጫ ተሸላሚ በመሆኑ የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ይህ ሽልማት ውጤት የአንድና የሁለት ሰራተኛ ውጤት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ውጤት በመሆኑ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!
የማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ልዩ ልዩ ሥራዎች
ትኩረት ለሴቶችና ሕፃናት ማህበር በዋናነት ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው አቅመ ደካማ ወላጆች ልጆችን በመንከባከብ ለሚሰጠው አገልግሎት ለሚያስገነባው ሕንፃ ብር 500000.00 /አምስት መቶሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል 100 ለሚሆኑ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሕፃናት አሳዳጊ አቅመ ደካማ እማወራ እና አባወራዎች ለእያንዳዳቸው አምስት ሊትር ዘይትና 10 ኪሎ ዱቄት እንዲሁም ለትንሳዔ በዓል 150 ለሚሆኑ ለእያንዳዳቸው 6 ሊትር ዘይት እና 10 ኪሎ ዱቁት በመለገስ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ አጠቃላይ በብር 492040/ አራት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ አርባ/ ወጪ በማድረግ የማዕድ ማጋራት ሥራ ተሰርቷል። አንዴ ማማ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገቢ የሌላቸውን ሴቶች በቀላሉ ከወዳደቁ ወረቀቶች ሊሰሩ የሚችሉ ጌጣጌጦችን እና መገልገያ እቃዎችን ሊያመርቱ እንዲችሉ ስልጠና በመስጠት ገቢ እንዲያገኙ በማስቻል ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፋብሪካው የተገለገለባቸውን ውድቅዳቂ ወረቀቶች እና ጊዜ ያለፈባቸውን ጋዜጦች እንዲሰጠው ጠይቆ በተፈቀደው መሠረት 438.10 ኪሎ.ግ ጋዜጣ እና የማያገለግሉ ወረቀቶች እንዲረከብ ተደርጓል::